የጡት ካንሰር ህመም ምልክቶች


1. በጡት ላይ እና በጡት አካባቢ የሚወጣ እባጭ አብዘኛውን ግዜ የጡት ካንሰር ህመም ምልክት የሚሆነው ህመም የለሽ የሆነ እባጭ ነው፡፡ ይህ እባጭ አብዛኛውን ግዜ ወደ ሰውነት የሚሰራጭ የካንሰር አይነት ላይሆን ይችላል፡፡ ነገር ግን ወደ ህክምና ተቋም በመሄድ ማረጋገጥ ተገቢ ነው፡፡

2.
የጡት መጠን እና ቅርጽ መለያየት አንዱን ጡት ከሌላኛው ጋር በማነጻጸር የቅርጽ እና የመጠን ልዩነት ካስተዋሉ ወደ ህክምና ተቋም በመሄድ ማረጋገጥ ተገቢ ነው፡፡

3.
በተወሰነ የጡት ቆዳ ላይ የመጠንከር ስሜት መከሰት 4.የጡት ጫፍ ወደ ውስጥ መገልበጥ ይህ አይነት የጡት ጫፍ ወደ ውስጥ መገልበጥ ከልጅነት (ቀድሞ የነበረ) ወይም
ተፈጥሮአዊ የሆነውን የጡት ጫፍ መገልበጥ አያካትትም

4.
የህመም ስሜት አልፎ አልፎ በጡት አካባቢ የህመም ስሜት ሊኖር ይችላል ፡፡ ነገር ግን የጡት አካባቢ ህመም በአብዛኛው የካንሰር ህመም ቀዳሚ መገለጫ ወይም ምልክት ላይሆን
ይችላል፡፡ የጡት ካንሰር ህመም የሚሰራጭባቸው ቦታዎችን የሚከተል የህመም ምልክት ሊኖረው ይችላል፡፡ ቀድሞ የሚሰራጨው ወደ ብብታችን ስር በሚገኘው( Lymph node ) በተላበው አካባቢ
ሲሆን ይህም የብብት ስር እብጠትን ሊስከትል ይችላል፡፡ የጡት ካንስር ቅድሚያ ካልተደረሰበት እና ህክምና ካላገኘ ወደ ጉበታችን እንዲሁም ወደተለያዩ የሰውነት ክፍሎች በመሰራጨት እስከ ሞት ሊያደርስ የሚችል የህመም አይነት ሲሆን በሀገራችን ኢትዮጵያም እየተበራከተ ያለ የህመም አይት ነው፡፡ በመሆኑም ከላይ የተጠቀሱትን ማናኛውም አይነት የህመሙ ምልክቶች የታዩት ሠው ወደ ህክምና ተቋም በመሄድ በቶሎ መፍትሄ ማግኘት ይኖርበታል፡፡
የጡት ካንሰር ህመም ምልክቶች የጡት ካንሰር ህመም ምልክቶች Reviewed by andbirr on 9:50 PM Rating: 5

No comments:

'; (function() { var dsq = document.createElement('script'); dsq.type = 'text/javascript'; dsq.async = true; dsq.src = '//' + disqus_shortname + '.disqus.com/embed.js'; (document.getElementsByTagName('head')[0] || document.getElementsByTagName('body')[0]).appendChild(dsq); })();
Powered by Blogger.